Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

ለቤት ፈላጊዎች መስፈርትና የምዝገባ መመሪያ ይፋ መደረጉ ተገለጸ

የአዲስ አበባ መስተዳድር በተለያዩ የቤት ልማት ፕሮግራሞች ለሚያስገነባቸው ቤቶች ከሰኔ ወር ጀምሮ ምዝገባ እንደሚያካሄድ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ መስተዳደሩ ባዘጋጀው አራት አይነት የቤቶች ልማት ፕሮግራም የከተማው ነዋሪ እንደፍላጎቱና እንደገቢው መጠን የቤት ባለቤት ለማድረግ ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን አስታውል፡፡

የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ አስተዳደር ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ኃይለማሪያም በበኩላቸው 10/90 20/80 40/60 እና የህብረት ስራ ማህበራት የቤት ልማት ፕሮግራሞች መዘጋጀታቸውን ገልዋል፡፡

10/90 ቤቶች ልማት ፕሮግራም በዝቅተኛ የገቢ ደረጃ የሚገኙ የከተማይቱ ነዋሪዎችን ታሳቢ ያደረገ ሲሆን በዚህ ፕሮግራም በመጀመሪያ ዙር 24 ሺህ ቤቶች እንደሚገነቡ አቶ ጌታቸው ገልጸዋል፡፡
ኮንዶሚኒየም በመባል የሚታወቀው 20/80 ቤቶች ልማት ፕሮግራምም ነባር እና አዲስ በመባል ምዝገባ እንደሚካሄድ ተገልጾ ከዚህ ቀደም ተመዝግበው ቤት ያላገኙ ሰዎች እንደገና የማጣራት ምዝገባ እንደሚካሄድም ተጠቁል፡፡

በ20/80 ቤቶች ልማት ፕሮግራም ቀደምት ተመዝጋቢዎች ከአዲስ ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው አቶ ጌታቸው ገልጸዋል፡፡
10/90 እና 20/80 ቤቶች ልማት ፕሮግራሞች ምዝገባ ከሰኔ 3 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 21 ድረስ በሁሉም ወረዳዎች እንደሚካሄድ ተጠቁል፡፡

40/60 ምዝገባ ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመረጡ ቅርንጫፎች ከነሀሴ 5 እስከ 17 የሚካሄድ መሆኑ ተገልል።

በመስሪያ ቤት፣ በመኖሪያ አካባቢ እና በውጪ የሚኖሩ እና በማህበር ለሚደራጁ ደግሞ ምዝገባው ከሀምሌ 15 እስከ 30 እንደሚካሄድ ተገልል፡፡

በማህበር የሚደራጁ የቤት ፈላጊዎች መሬት ከሊዝ ነፃ የሚሰጥ ሲሆን የተነሺዎች ካሳን ግን ማህበሩ የሚሸፍን መሆኑ ተጠቁል፡፡

ቤቶቹ በቤቶች ልማት ኤጀንሲ የሚገነባ ሲሆን ማህበራቱ የወጪውን 50 በመቶ በምዝገባ ወቅት ቀሪውን 50 በመቶ ደግሞ የግንባታ ፍቃድ ከመሰጠቱ በፊት ከፍለው ማጠናቀቅ እንደሚጠበቅባቸው ተገልል።

የመንግስት ሰራተኞች ለነሱ ብቻ በተዘጋጀ የተለየ መመዝገቢያ ቦታ ምዝገባው የሚካሄድ መሆኑ ተገልል፡፡

መስተዳድሩ ባካሄደው ጥናት መሰረት 600ሺህ ያህል የከተማዋ ነዋሪዎች ሊመዘገቡ እንደሚችሉ የተናገሩት አቶ ጌታቸው መስተዳደሩ ግን 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሰዎች ያህል ሊመዘገብ እንደሚችል ከወዲሁ አስታውል፡፡

የምዝገባ አፈፃፀም ሥነ-ሥርዓት
-    ዕድሜያቸው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ
-    በከተማዋ ውስጥ ቢያንስ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የኖረና እየኖረ ያለ
-    የከተማዋ ነዋሪ ሆኖ ነገር ግን ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በሥራ ወይም በትምህርት ምክንያት ከከተማዋ ውጪ የኖረበትን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና ማስረጃው ቦታውን ለምን ያህል ጊዜ እንደቆየ ወይም እንደሚቆይ በዝርዝር ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

10/90 (አነስተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች)

-    በየወሩ ብር 187 ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ሳይቋረጥ በተከታታይ  2 ዓመታት መቆጠብ ይኖርባቸዋል።
-    ስለ ገቢ መጠናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል
20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት (ነባር)
ከምዝገባ ቀን ጀምሮ በየወሩ ለተከታታይ 5 ዓመታት መቆጠብ የሚኖርበት

-    ለባለ 3 መኝታ ቤት ብር 685
-    ለባለ 2 መኝታ ቤት ብር 561
-    ለባለ 1 መኝታ ቤት ብር 274
-    ለስቲዲዮ መኝታ ቤት ብር 151

20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት (አዲስ)

-    ለባለ 3 መኝታ ቤት ብር 489
-    ለባለ 2 መኝታ ቤት ብር 401
-    ለባለ 1 መኝታ ቤት ብር  196
40/60 የቤቶች ልማት ፕሮግራም

-    ለባለ 3 መኝታ ቤት  ብር 2453
-    ለባለ 2 መኝታ ቤት ብር 1575
-    ለባለ 1 መኝታ ቤት ብር  1033

 

 

 

 

 

 
Amharic (Ethiopia)
የአዲስ አበባ ገፅታ
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa
 • Addis Ababa